Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ከፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ከ1 ሺህ 700 በላይ የዞንና የወረዳ አመራሮችና ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባሳለፍነው ወር ተፈጥሮ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ በተለያዩ የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ።

የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ እርምጃው የተወሰደው ከመንግስት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ባልቻሉ እና በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ውስጥ ተሳትፈዋል በተባሉ ሰራተኞች ላይ ነው።

በዚህም መሰረት እርምጃው ከ500 በላይ በመሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ላይ እንዲሁም ከ1 ሺህ 200 በላይ በሚሆኑ የዞን፣ የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች ላይ መወሰዱን ቢሮው አስታውቋል።

በክልሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የመንግስት ሰራተኞች ላይ የተወሰደው እርምጃ የህግ እና የፖለቲካ መሆኑም ነው የተገለፀው።

ቢሮው በመግለጫው አክሎም፥ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት ውስጥ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩት ከ500 በላይ የመንግስት ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑንም አስታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል የህግ የበላይነትን ማስከበር ላይ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ባካሄደው ኮንፍረንስ መወሰኑንም ቢሮው በመግለጫው አስታውሷል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.