Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ ከ9 ሺህ በላይ ሲም ካርድ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ 9 ሺህ 375 ሲም ካርድን ጨምሮ የተለያየ ቁሳቁስ መያዙን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው ኃላፊ ኮማንደር ፉፋ መገርሳ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ ከሲም ካርዶቹ በተጨማሪ 1 ሽጉጥ፣ 5 ላፕቶፕ ኮምፒዩተር፣ ሀሰተኛ መታወቂያና የሸኔ አርማዎች ከነ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛሉ፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል አሸባሪዎቹ ሸኔና ህወሓት የሽብር ድርጊት እንዲፈጽሙ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ድርጊት ተሳትፎ ሳያድረጉ እንዳልቀሩ የተጠረጠሩ መያዛቸውን ኮማንደሩ ተናግረዋል፡፡
ይህ ውጤት የተገኘው በተለያዩ የጸጥታና ህዝባዊ መዋቅር፣ ከከተማው ነዋሪ፣ ከአጎራባች ዞኖች፣ ወረዳዎችና ክልሎች ጋር በቅንጅትና በመናበብ በተሰራው ስራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.