Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በልግ አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች ከ900 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሰብሎች ተሸፍኗል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በልግ አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች 970 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማት ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ እንደገለፁት÷የዘንድሮው የበልግ ዝናብ ዘግይቶ ቢጀምርም ቀድሞ የእርሻ ማሳ ዝግጅት በመደረጉና 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል የፋብሪካ ማዳበሪያን ጨምሮ የምርጥ ዘር አቅርቦት አርሶ አደሩ እጅ እንዲደርስ በመደረጉ ውጤታማ መሆን መቻሉን ተናግረዋል።

የበልግ እርሻው እቅድ ሙሉ በሙሉ መሳካቱን የገለፁት ምክትል ሃላፊው÷ በልግ አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች ስንዴ፣ ገብስ፣ ቦቆሎን ጨምሮ የተለያዩ የአገዳ ሰብሎችና ጥራጥሬ መዘራቱን አመልክተዋል።

በዚህም ከ30 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት መታቀዱንና በአሁኑ ወቅት የዝናብ ስርጭቱ በደጋማ የክልሉ አካባቢዎች በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን ምክትል ሃላፊው መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.