Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በመጭው ክረምት የሚተከሉ ከ4 ቢሊየን በላይ ችግኞች እየተዘጋጁ ነው

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመጭው ክረምት የሚተከሉ ከ4 ቢሊየን በላይ ችግኞች እየተዘጋጁ መሆኑን የኦሮሚያ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
በቢሮው የደን ልማትና እንክብካቤ ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ለማ ÷በክልሉ የሚተከሉ 4 ነጥብ 1 ቢሊየን ችግኞች እየተዘጋጁ ነው ብለዋል።
እየተዘጋጁ ያሉት ችግኞች የደንና የምግብነት ዝርያ ያላቸው የዛፍ አይነቶች መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ችግኞቹ ሀገር በቀል ዛፎችን ጨምሮ የፍራፍሬ፣ የቀርከሃና ለእንስሳት መኖ የሚውሉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ለተከላ ከታቀዱት ችግኞች ውስጥ እስካሁን 74 በመቶው የማፍላት ስራ መከናወኑንም አመላክተዋል።
ችግኞቹ በአርሶ አደሩ ማሳ፣ በማህበራትና በመንግስት ጣቢያዎች እየተዘጋጁ ሲሆን፥ እየተዘጋጁ ያሉት ችግኞችም 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት የመሸፈን አቅም እንዳላቸው አውስተዋል።
በችግኝ ዝግጅቱ የስራ እድል የተፈጠረላቸው 58 ሺህ ዜጎች ከ172 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ እንዳገኙ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በክልሉ ባለፈው ክረምት 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸው ታውቋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.