Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የሶማሊኛ ቋንቋ እንደ ተጨማሪ የቋንቋ ትምህርት መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የሶማሊኛ ቋንቋ እንደ ተጨማሪ የቋንቋ ትምህርት መሰጠት ተጀመረ።
በቅርቡ የሶማሌና የኦሮሚያ ክልል አመራሮች በኦሮሚያ ክልል እና የሶማሌ ክልል ትምህርት ቤቶች የሱማሊኛና የአፋን ኦሮሞ ቋንቋን ለመስጠት መስማማታቸው ይታወሳል፡፡
በያተያዘው እቅድ መሰረትም ዛሬ የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ መሀመድ ፋታህ፣ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ግርማ ባይሳ እና ሌሎች የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል አመራሮች በኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጭናክሰን ወረዳ የዋሊድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የሶማሊኛ ቋንቋ ትምህርትን አስጀምረዋል።
በዚህ ወቅትም የስራ ሃላፊዎቹ የቋንቋው መሰጠት መጀመር የህዝቡን ትስስር የሚያጠናክር ነው ብለዋል።
በኦሮሚያ ክልል በ11 ትምህርት ቤቶች የሶማሊኛ ቋንቋ እንደተጨማሪ ቋንቋ ትምህርት በመሰጠት ላይ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ግርማ ባይሳ መናገራቸውን የሶማሌ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.