Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በኦነግ ሸኔ እና በህወሓት ጽንፈኞች ላይ እየተወሰደ ባለው እርምጃ 67 ታጣቂዎች ተደምስሰዋል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በኦነግ ሸኔ እና በህወሓት ጽንፈኞች ላይ እየተወሰደ ባለው እርምጃ 67 ታጣቂዎች ሲደመሰሱ ፤ 30 ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ፤በክልሉ ህግ የማስከበር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በቅርቡ በምእራብ ወለጋ የበርካቶችን ህይወት የነጠቀው ጥቃት ላይ የተሳተፉ ሀይሎች ላይ የኦሮሚያ ክልል ህግን እያስከበረ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንደገለፀው ጥፋቶቹ እየተፈፀሙ ያሉት በኦነግ ሸኔ እና በህወሓት ቡድን ተልእኮ ተሰጥቷቸው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ሲሆን እነዚህን የሰው ልጅ ጨፍጫፊ ቡድኖችን ለመደምሰስም ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።
ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ በጥፋት ሀይሎቹ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ እና ህግን የማስከበር ስራም በስፋት እየተከናወነ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
ጥቃት የተፈፀመባቸው የክልሉ አከባቢዎች አሁን ላይ ወደ አንፃራዊ ሰላም መመለሳቸውን ነው ኮሚሽነሩ የሚናገሩት።
እስካሁንም በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች በተለይም በምእራብ ወለጋ በተሰራው ህግ የማስከበር ተግባር 67 የሚሆኑ ታጣቂዎችን መደምሰስ የተቻለ ሲሆን ከ30 በላይ የሚሆኑትን ደግሞ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ነው ያሉት ።
ሁለቱ የጥፋት ቡድኖች ክልሉን ለማተራመስ በስፋት አየተንቀሳቀሱ መሆኑን ከሚታዩት ማሳያዎች በተጨማሪ በክትትል የተደረሰባቸው መሆኑን የሚያነሱት ኮሚሽነር አራርሳ እየተወሰደ በሚገኘው እርምጃ በርካታ የጦር መሳሪያዎችንም መያዝ ተችሏልም ብለዋል።
ህብረተሰቡም እነዚህን ቡድኖች አሳልፎ የመስጠት ተግባሩን አጠናክሮታል ነው የሚሉት።
በዙፋን ካሳሁን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.