Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ደሎ መና ወረዳ የኮሌራ ወረርሽኝ ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ደሎ መና ወረዳ የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ፡፡
ችኩንጉኒያ ወረርሽኝም በድሬደዋ ሱማሌ እንዲሁም በአፋር ክልሎች ሊከሰት እንደሚችል የኢንስቲትዩቱ የበሽታዎች ቅኝት እና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ መስፍን ወሰን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል።
የአየር ጠባይን ተከትሎ የሚከሰት ወረርሽኝ ሊኖር ስለሚችል ህብረተስቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
ከመሀል አዲስ አበባ በስተቀር በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በደቡብ ክልሎች የአየር ጠባይን ተከትሎ የወባ ወረርሽኝ ሊከሰት ስለሚችል ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን እና አካባቢዎች በማጽዳት ህብረተስቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
ከጤና ሚኒስቴር እና ከክልሎች ጤና ቢሮ ጋር በመነጋገር ስጋት ያለባቸውን ቦታዎች የመለየት ስራ እየተሰራ እንደሆነ ጠቅሰው÷ ወረርሽኙ ቢከስት አስፋላጊው ግብዓቶችን ለማቅረብ መዘጋጀታቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
በሲሳይ ጌትነት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.