Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዕውቅናና የሽልማት መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2013 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ውጤት ላመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዕውቅናና የሽልማት መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡
በክልሉ በ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 253 ሺህ ተማሪዎች መካከል 226ቱ እጅግ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገባቸው በዛሬው ዕለት ዕውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡
የክልሉ ርዕስ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳም ለተማሪዎቹ ሽልማቱን ሰጥተዋል።
በተመሳሳይ በዛሬው መርሐ ግብር ለቡኡረ ቦሩ ትምህርት ቤት ፕሮጀክት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡
በክልሉ 3 ሺህ የቡኡረ ቦሩ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ፥ 3 ሺህ 377 ትምህርት ቤቶች ግንባታ የተጀመረ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ 3 ሺህ 11 ያህሉ ግንባታቸው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተገልጿል፡፡
የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ የሚከናወነው ከተለያዩ ተቋማት እና ከማህበረሰቡ በተሰበሰበ 12 ቢሊየን ብር መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በያዴሳ ጌታቸው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.