Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከ40 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መዘጋጀቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በኦሮሚያ ክልል ከ40 ነጥብ 9 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መዘጋጀቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ ።
የቢሮው ኃላፊ አቶ አበራ ወርቁ÷ በተያዘው 2014/15 የምርት ዘመን የፋብሪካ ማዳበሪያ ዋጋ በመናሩ የግብርና ምርትና ምርታማነት ላይ እጥረት እንዳያጋጥም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የፋብሪካ ማዳበሪያ እጥረትን በተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማካካስ በክልል ደረጃ ከ54 ሚሊየን በላይ ሜትር ኪዩብ ለማዘጋጀት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው÷ እስካሁን ባለው ሂደትም ከ40 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መዘጋጀቱን ነው ለለኢዜአ የገለጹት፡፡
የፋብሪካ ማዳበሪያ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መናሩን የገለፁት አቶ አበራ÷ በግብርናው ዘርፍ የፋብሪካ ማዳበሪያ እጥረትን እንደ ቁልፍ ችግር ወስደን እየሰራንበት ነው ብለዋል።
በክልሉ የግብርና ምርትና ምርታማነት ላይ ተፅዕኖ እንዳይኖር የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅቱን አጠናክረን አስቀጥለናል ያሉት ኃላፊው÷ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ከባዮ ጋዝ ተረፈ ምርቶችና መደበኛ የተፈጥሮ ማዳበሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን አመላክተዋል።
በክልሉ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በበልግና የበልግ መስኖ ልማት ለመሸፈን ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.