Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ዘመናዊ የኢኮኖሚ ዞን ለመገንባት በተዘጋጀ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ዘመናዊ የኢኮኖሚ ዞን ለመገንባት በተዘጋጀ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ።

ዘመናዊ ከተማው “ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን ፕሮጀክቱን ዕውን ለማድረግ በተዘጋጀው ጥናት ላይ ውይይት ተካሂዷል።

የፕሮጀክቱ አላማ ሁሉን አቀፍ ዘመናዊ ከተማ መገንባት ነው ተብሏል።

ሀሳቡ ባለፈው አመት ለክልሉ የካቢኔ አባላት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት ነበር።

ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግም ዕቅድ እና ጥናቱ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበታል።

ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በውስጡ ሁሉን የልማት ፍላጎቶች ያካተተ እና ዘመናዊ ከተማ የሚፈጥር ነው መሆኑም ነው የተገለጸው።

የባህል ማዕከል እና የቱሪዝም ምርት በዘመናዊ ከተማው ከሚካተቱት መሀል ጥቂቶቹ መሆናቸውን የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ገልጿል።

በፕሮጀክቱ የመኖሪያ መንደሮች፥ መዝናኛ ስፍራዎች፥ ኢንዱስትሪ ዞን፥ ሎጅስቲክስ፥ ደረቅ ወደብ፥ መጋዘኖች እና የተለያዩ አገልግሎቶች የተካተቱ ሲሆን በሂደት በ40 አመታት የሚፈጸም መሆኑም ነው የተገለጸው።

ክልሉ “በቤተሰብ ደረጃ ብልጽግናን ማረጋገጥ” የሚያስችሉ በርካታ ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ እያስገባ ይገኛልም ብሏል ፓርቲው።

ፕሮጀክቱ በ23 ሺህ 556 ሄክታር ላይ የሚገነባ ሲሆን ለበርካታ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊነት የስራ ዕድል ይፈጥራል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.