Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ህዝብ ለመከለከያ ሰራዊት 33 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አሸባሪው ህወሓትና ተላላኪውን ሸኔ በግንባር በመፋለም ላይ ለሚዘጋጁ ጀግኖች 33 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የዞኑ አስተዳዳሪና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አብርሃም ጋዲሣ እንደገለጹት ÷ የዞኑ ሕዝብ አሸባሪውን ህወሓት በግንባር እየተፋለሙ ለሚገኙ ጀግኖች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

በዞኑ 13 ወረዳዎች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች፣ አርሶ አደሮች፣ ነጋዴዎችና ባለሀብቶች ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥም 33 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በተለይ አርሶ አደሮች የምግብ እህል በማዋጣት በሬዎችን፣ በግና ፍየሎችን በግንባር ጠላትን በመፋለም የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም በርካታ ነዋሪዎችን ያሳተፈ የሞራልና የደም ልገሣ ፕሮግራም እንደሚካሄድም የኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ ገልፀዋል፡፡

የዞኑ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት የሚሊሻ አባላት ፣ ወላጆችና ቤተሰቦች እንዲደገፉ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም በአሸባሪው ህወሓት እኩይ ድርጊት ሳቢያ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ለመድረስ የዞኑ ሕዝብ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ነው ያመለከቱት፡፡

ኢዜአ ያነጋገራቸው የፍቼ ከተማና የግራር ጃርሶ ወረዳ ነዋሪዎች እንዳሉት ፥ አሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ በግንባር በመፋለም ሰራዊቱ መተኪያ የሌለውን ሕይወቱን በመክፈል የሀገር ህልውና ለማስከበር ለሚከፍለው ጥረት ድጋፍ እያደረጉ ነው፡፡

አሸባሪው ህወሓትና ተላላኪው ሸኔ እስኪጠፉ ባላቸው አቅም ሁሉ እስከ መጨረሻው ለመታገል እንደተዘጋጁም አመልክተዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.