Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ከ14 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የዋጋ ንረት በማባባስ የኑሮ ውድነት እንዲፈጠር ባደረጉ 14 ሺህ 662 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

እርምጃው የተወሰደው ሀገሪቱ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በመጠቀም ሰው ሠራሽ የኑሮ ውድነት የሚፈጥሩ ሰዎችን ለማስቆም መሆኑን የክልሉ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ዴንጌ ቦሩ ተናግረዋል።

እስካሁን 166 ሰዎች ላይ ክስ መመሥረቱን እና 14 ሰዎች ከ6 ወር እስከ 2 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑንን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

ሕብረተሰቡ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ የግብርና እና የፋብሪካ ምርቶች አውደ ርዕይና ባዛር በክልል ደረጃ መዘጋጀቱንም ኦ ቢ ኤንን ዋቢ ያደረገው የኢትዮጵያ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.