Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል 10 ነጥብ 6 ሚሊየን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል 10 ነጥብ 6 ሚሊየን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለሳቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ ገለፁ፡፡

በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት በመቋረጡ ተማሪዎች ለድብርት፣ ፆታዊ ጥቃት እና ያለዕድሜ ጋብቻ እንዳይጋለጡ ስጋት እንደነበረ አስረድተዋል፡፡

ስለዚህም ትምህርትን በጥንቃቄ ማስቀጠል አማራጭ የሌለው መሆኑን ጠቅሳዋል፡፡

በክልሉ በመጀመሪያ ዙር በ8ኛ ክፍል የተጀመረው ትምህርትን የማስቀጠል ስራ በአሁኑ ወቅት በሁሉም ደረጃ ያሉ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

የቫይረሱን ስርጭት ስጋት ለመከላከል 20 ሚሊየን ማስክ ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ እንዳለ ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት 7 ሚሊየን እየተሰራጨ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ከ230 ሺህ መምህራን ጋር ኮሮናን ስለመከላከል፣ ትምህርት ጥራት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይት መካሄዱንም አስታውቀዋል፡፡

ባለፉት ወራት በክልሉ ለትምህርት ዝግጅት በተደረገበት ወቅት 30 ሺህ ተጨማሪ የማስተማሪያ ክፍሎች መገንባታቸውን ነው ያነሱት፡፡

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ታርሞ እየተጠናቀቀ መሆኑን በመጥቀስም ውጤቱ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ቤተሰብ፣ መምህራን፣ ተማሪዎች እና በየደረጃው ያለ አመራር ለተማሪዎች ደህንነት፣ ጤና እና ከኮሮናቫይረስ መጠበቅ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.