Fana: At a Speed of Life!

በከተማዋ ያለውን የመሬት ወረራ በተመለከተ የተካሄደውን ግምገማ የተመለከተው ሪፓርት በአንድ ሳምንት ውስጥ ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የመሬት ወረራ ጥቆማ እና ቅሬታዎች ለማጣራት የተቋቋመው ግብረ ኃይል የስራ አፈፃፀም እና ግኝቶች በዛሬው ዕለት መገምገሙ ተገለፀ።

በግምገማው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ዣንጥራር አባይ ተገኝተዋል።

ግምገማው የተካሄደው የከተማ አስተዳደሩ መረጃዎችን እና በመሬት ላይ ያለውን እውነታ ማወቅ፣ ማረም እና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ታሳቢ በማድረግ መሆኑን ምክትል ከንቲባዋ ገልፀዋል።

አጠቃላይ ሪፖርቱ በአንድ ሳምንት ውስጥ ተጠናቆ ግኝቶቹ ለህዝቡ ይፋ የሚደረጉ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ተቋርጦ የነበረው የመሬት ነክ አገልግሎት እገዳ እንደሚነሳ ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.