Fana: At a Speed of Life!

በኩዌት፣ ባህሬን እና አፍጋኒስታን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ተገኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኩዌት፣ ባህሬን እና አፍጋኒስታን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል።

መነሻውን ከወደ ቻይና ውሃን ግዛት ያደረገው የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ከቻይና ውጭ በርካታ ሃገራትን እያዳረሰ ነው።

በዚህም በኩዌት ሶስት እንዲሁም በባህሬን እና አፍጋኒስታን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን የየሃገራቱ የጤና ሚኒስቴሮች አስታውቀዋል።

በትናንትናው እለትም በቻይና 150 እንዲሁም በደቡብ ኮሪያ 70 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተገልጿል።

በኢራን 43 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን እስካሁን 12 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

ይህን ተከትሎም ቱርክ፣ ፓኪስታን እና አርሜኒያ ከኢራን ጋር የሚያዋስናቸውን ድንበር ዘግተዋል፤ አፍጋኒስታንም የጉዞ እገዳ ጥላለች።

በጣሊያን ወደ 150 የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፥ አራት ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውም ተገልጿል።

የኮሮና ቫይረስ እስካሁን ዓለም ላይ ከ2 ሺህ 600 በላይ ሰዎችን ለህልፈት ሲዳርግ የስርጭት አድማሱም እየተስፋፋ ይገኛል።

ምንጭ፡-አልጀዚራ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.