Fana: At a Speed of Life!

በካፋ ዞን ሃይማኖታዊ ቅርሶችን ለመጠገን 300 ሚሊየን ብር ተመደበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በከፋ ዞን የሚገኙ ሶስት ሃይማኖታዊ ቅርሶችን ለመጠገን 300 ሚሊየን ብር ተመድቧል።

በዞኑ የአንድራቻ መድሃኒዓለም፣ የበሃ ጊዮርጊስ እና የቶንገላ አብዱሰላም መስጂድ ቅርሶች ካላቸው የዕድሜ ብዛት አንጻር ለአደጋ መጋለጣቸውን የተቋማቱ አስተዳዳሪዎች ገልፀዋል።

የአንድራቻ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መላከ መዊ ሰለሞን በላይ ፥ ቅርሱ ውሃ ወደ ውስጥ ማስረግ በመጀመሩ አደጋ ላይ እንደወደቀ ጠቅሰው ፥ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ከ600 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የቶንገላ አብዱሰላም መስጂድ አስተዳዳሪ ሼህ መሐመድ ከድር ስዲቅ በበኩላቸው ፥ ቅርሱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሊወድቅና ሊጠፋ ይችላል ብለዋል።

ሃይማኖታዊ ቅርሶች ይዘታቸውን ሳይለቁ ለመጠገን 300 ሚሊየን ብር መመደቡን የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የቅርስ ጥገናና እንክብካቤ ስራ ክፍል ሃላፊ ሰላማዊት ጌታቸው ናቸው፡፡

ከዞኑ ባህልና ቱሪዝም ጋር በተደረገው የውል ስምምነት መሠረት ገንዘቡ ወደ ዞኑ ሂሳብ ገቢ ሲደረግ ስራው ይጀመራል ነው ያሉት።

ቅርሶቹን ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ለማስጠገን ቅድመ ዝግጅት መጀመሩን ጠቅሰው ፥ ለስራ ምቹ ይሆን ዘንድ ክረምቱ ሲገባደድ ጥገናው እንደሚጀመር አስታውቀዋል።

በፍሬው ዓለማየሁ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.