Fana: At a Speed of Life!

በሕንድ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በኬንያ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  በሕንድ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በኬንያ በአምስት ሰዎች ላይ መገኘቱ ተሰማ፡፡
የኬንያ የጤና ሚኒስቴር እንደገለጸው ቫይረሱ ከህዝብ በተወሰደ ናሙና የተገኘ ነው፡፡
ምርመራውም ወደ ህንድ የሚደረግ በረራ ከመታገዱ በፊት የተደረገ ነው ብሏል፡፡
ቫይረሱ የተገኘባቸው አምስት ሰዎች በምዕራባዊ የሃገሪቱ ክፍል በሚገኝ የማዳበሪያ ፋብሪካ ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በዚህም ኬንያ አሁን ከኡጋንዳ ቀጥላ በህንድ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ የተገኘባት ሁለተኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆናለች፡፡
ህንድ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ እጅግ በከፋ የኮሮና ቫይረስ ማዕበል ውስጥ ስትሆን በየቀኑ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ለህልፈት በመዳረግ ላይ ናቸው፡፡
ኬንያ በቫይረሱ ሳቢያ ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ህንድ የሚደረጉ በረራዎችን ለጊዜው ማገዷ ይታወሳል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.