Fana: At a Speed of Life!

በኬንያ ከ900 በላይ የህክምና ባለሙያዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተነገረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኬንያ ከ900 በላይ የህክምና ባለሙያዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተነገረ።

በሀገሪቱ ቫይረሱ ከተከሰተ ጀምሮ እስከ አሁን 945 የህክምና ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

16 የህክምና ባለሙያዎችም በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው።

የኬንያ መንግሥት ቀደም ሲል ህክምና ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸው አይቀሬ ነው ሲል ተናግሮ ነበር።

ሆኖም ሚኒስቴሩ መንግስት የሙያ ግዴታቸውን ሲወጡ ራሳቸውን ከቫይረሱ መከላከል እንዲችሉ የሚረዱ ቁሳቁሶችን ለማሟላት እና ሰራተኞቹን ከቫይረሱ ለመጠበቅ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

በሀገሪቱ በአጠቃላይ 36 ሺህ 576 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፥ 642 ሰዎች በቫረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል።

23 ሺህ 611 የሚሆኑት ደግሞ ቫይረሱ ማገገም ችለዋል።

ምንጭ፦ ሲ.ጂ.ቲ.ኤን

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.