Fana: At a Speed of Life!

በኬፕ ታወን ከተማ በሚገኘው ቴብል ተራራ የተቀሰቀሰው እሳት ታሪካዊ ህንፃዎችን አወደመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካዋ የመስህብ ከተማ ኬፕታወን በሚገኘው ቴብል ተራራ የተቀሰቀሰው እሳት ታሪካዊ ህንፃዎችን ማውደሙ ተገለፀ።

በቴብል ተራራ ላይ የተቀሰቀሰው እሳት በአቅራቢያው ወደ ሚገኘው ኬፕ ታወን ዩኒቨርሲቲ ግቢ የተዛመተ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል።

በትናንትናው ዕለት ረፋድ ላይ የተቀሰቀሰው እሳት በፍጥነት  እንደተስፋፋ እና ምግብ ቤቶችንም እንዳወደመ ተነግሯል።

በኬፕ ታወን ዩኒቨርሲቲ ግቢ የሚገኙ ታሪካዊ ቤተ መፅሐፍት እና ህንፃዎችም ጉዳት እንደደረሰባቸው ነው የተነገረው።

አራት ሄሊኮፕተሮች እና 120 የእሳት ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ፓርክ የእርጥበት ሁኔታው ዝቅተኛ መሆኑ እና ደረቅ ቁጥቋጦዎች እሳቱ በፍጥነት እንዲስፋፋ አድርጎታል ብሏል።

እሳቱ የራሱን ነፋስ መፍጠሩም የመዛመት ፍጥነቱን ከፍ እንዳደረገው በመግለፅ የእሳት አደጋ ባለሙያዎች እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ቢያንስ ሶስት ቀናት እንደሚያስፈልጋቸው ገልጿል፡፡ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.