Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ 13 ዞኖች የወባ በሽታ በስፋት እንደሚገኝ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወባ በሽታን ከክልሉ ለማጥፋት ዘርፈ ብዙ ስራዎች ቢሰሩም አሁንም በሽታው የህብረተሰቡ የጤና ችግር ሆኖ መቀጠሉን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ አስታወቀ ።

የወባ በሽታ በምስራቅ ሀረርጌ ፣ ምዕራብ ሀረርጌ ፣ አርሲ ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ አንዲሁም ሆሮ ጉዱሩ ወለጋን ጨምሮ በክልሉ 13 ዞኖች በስፋት አንደሚገኝም የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደረጀ አብደና ተናግረዋል።

ክልሉ በሽታውን ለማጥፋት የተሰሩ ስራዎችን በአዳማ ከተማ በገመገመበት ወቅት ጉዳዩ አሁንም ትኩረት እንደሚሻ ተነግሯል፡፡

በሀገር ደረጃ የወባ በሽታን ለማጥፋት የተያዘውን እቅድ ባማከለ መልኩ በኦሮሚያ ክልል የተሰራ ስራ ቢኖርም የተፈለገውን ውጤት ማምጣት አልተቻለም ብለዋል አቶ ደረጀ።

የአመራር ትኩረት ማጣት፣ የመመርመር አቅም ማነስ፣ የአቅርቦት ችግርና የስራ ጥራት ማጣት ለአፈፃፀሙ ዝቅተኛ መሆን እንደምክንያት ተጠቅሰዋል።

ይህንን ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት ፈጣን የስድስት ወራት ዕቅድ ወጥቶ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ደረጀ ተናግረዋል ።

የህክምና ግብአት እጥረትን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ማህበራዊ መሰረት እንዲኖረውም ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ መሆኑን ነው ያስረዱት።

በይድነቃቸው ኃ/ማርያም

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.