Fana: At a Speed of Life!

በክልሎች የተፋሰስ ልማት ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ክልሎች የተፋሰስ ልማት ስራ ተጀመረ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ለ45 ቀናት የሚቆይ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ሥራ መጀመሩን የዞኑ የእርሻ እና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የጽህፈት ቤቱ ተወካይ አቶ ጀቤሣ ደገፋ እንደገለጹት የልማት ሥራው የተጀመረው በዞኑ ሰዲ ጫንቃ ወረዳ ውስጥ ነው፡፡

የዘንድሮው በጋ ወራት በዞኑ በሚገኙ 12 ወረዳዎች  በተመረጡ 266 ተፋሰሶች ውስጥ 117 ሺህ 366 ሄክታር መሬት የሚሸፍን የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ እንደሚካሄድም ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም 11 ሺህ 957 ሄክታር መሬት ከሰውና ከእንስሳት ንክኪ የመከለል ሥራ እንደሚሰራም አስረድተዋል፡፡

በዞኑ ቀድሞ የተጀመረው የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ሥራ በአሮሚያ ክልል ደረጃ ከነገ  ጀምሮ ይቀጥላል ተብሏል፡፡

በተያያዘም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ህብረተሰቡን በማሳተፍ በዘመቻ የሚካሄድ ዓመታዊ የበጋ ተፋሰስ ልማት ሥራ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

የልማቱን ሥራ በክልሉ አሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ በመገኘት ያስጀመሩት የክልሉ ርዕስ መስተዳድር ተወካይ አቶ ባበክር ከሊፋ ናቸው።

በክልሉ አባይ ተፋሰስ አካባቢ የተራቆቱ መሬቶች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል የተባለው ዘመቻ ለሁለት ወራት እንደሚቆይ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.