Fana: At a Speed of Life!

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወደመ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ እንደገለጹት÷ አደጋው የተከሰተው ዛሬ ማለዳ ከጠዋቱ 1 ሰአት ከ30 በክፍለ ከተማው ወረዳ አራት ዓለም ባንክ አደባባይ አካባቢ ነው።
በእሳት አደጋውም 150 ካሬ ሜትር በሚሸፍኑ አምስት ሱቆች ላይ ቃጠሎ መድረሱን ገልጸው÷ በደረሰው አደጋ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት መውደሙን ተናግረዋል።
የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር በተደረገው ርብርብ ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ማትረፍ ተችሏል ነው ያሉት።
በአደጋው ሳቢያ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አመለኖሩን የጠቀሱት አቶ ጉልላት የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
እሳቱን ለማጥፋት 40 ደቂቃ የፈጀ ሲሆን 85 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና ስምንት ከባድ ተሽከርካሪዎች መሰማራታቸውን በመጥቀስ፤የአዲስ አበባ ፖሊስና የአካባቢው ማህበረሰብ እሳቱን ለማጥፋት ትብብር ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።
በቀጣይ ተመሳሳይ አደጋዎች አንዳይከሰቱ ሕብረተሰቡ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅበትም ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.