Fana: At a Speed of Life!

በኮሎምቢያ ማረሚያ ቤት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በተነሳ አመፅ ከ23 ሰዎች በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሎምቢያ ማረሚያ ቤት ከኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ጋር በተያያዘ በተቀሰቀሰ አመፅ ከ23 ሰዎች በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ።

አመፁ በመዲናዋ ቦጎታ በሚገኝ ትልቅ ማረሚያ ቤት ውስጥ የተነሳ ሲሆን፥ ከሞቱት በተጨማሪ 83 እስረኞች መቁሰላቸውን የሃገሪቱ ፍትህ ሚኒስትር አስታውቀዋል።

አመፁ በማረሚያ ቤቱ ከመጠን በላይ መጨናነቅ እና ደካማ የጤና አጠባበቅ ስርአት አለ በሚል መቀስቀሱም ነው የተገለጸው።

የፍትህ ሚኒስትሯ ማርጋሪታ ሳቤሎ ድርጊቱ በሃገሪቱ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች የተቀነባበረ አመፅ በመቀስቀስ ረብሻ ለመፍጠር የተሞከረ ነው ብለዋል።

ከአመፁ ጋር በተያያዘም ሚኒስቴሩ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በኮሎምቢያ እስካሁን 231 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ ሁለት ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

ነገር ግን በቫይረሱ ሳቢያ እስካሁን በማረሚያ ቤቶች የተያዘ ሰው የለም ነው የተባለው።

 

ምንጭ፦  ቢቢሲ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.