Fana: At a Speed of Life!

በኮምቦልቻ ከተማ ማር ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅሎ ሲያዘጋጅ የተገኘ ግለሰብ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮምቦልቻ ከተማ በመኖሪያ ቤቱ ማር ከባዕድ ነገር ጋር በመቀላቀል ለሽያጭ ሲያዘጋጅ የተገኘ ግለሰብ በህብረተሰብ ጥቆማ እጅ ከፈንጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

በከተማ አስተዳደሩ የበርበሬ ወንዝ ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊ ኮማንደር ወንድዬ በላይ እንደገለጹት፥ እጅ ከፍንጅ የተያዘው ግለሰብ የአፈር ማዳበሪያ፣ ስኳር፣ ኬሚካሎችና ሌሎችንም ባዕድ ነገሮችን ከማር ጋር በመቀላቀል ሲያዘጋጅ ተደርሶበታል።

በዚህም ባለ 20 ሊትር 40 ባልዲ ከባዕድ ነገር ጋር የተቀላቀ ማር ለገበያ ለማቅረብ አዘጋጅቶ እንደነበር ገልጸዋል።

እንደኢዜአ ዘገባ ግለሰቡ ተጨማሪ ባዕድ ነገር የተቀላቀለበት ማር በማዘጋጀት ላይ እንዳለ ተደርሶበታል።

ለገበያ ሊቀርብ ከተዘጋጀው በተጨማሪም ግለሰቡ ከማር ጋር ለመቀላቀል የሚጠቀማቸው ባዕድ ነገሮች በጆንያና ሌሎች ቁሳቁሶች ውስጥ ተከማችተው እንደተገኙ ጠቁመዋል።
በቁጥጥር ስር ከዋለው ግለሰብ ጋር ተባብረው የሚሰሩ አካላትን ለመያዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ኮማንደር ወንድዬ አስረድተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን ሽመልስ በበኩላቸው፥ የተዘጋጀው ማር መሰል ባዕድ ነገር ወደ ገበያ ቢገባ በህብረተሰቡ ጤና ላይ ሊያስከትል ከሚችለው ጉዳት ሌላ ትክክለኛ ማር በሚያቀርቡ ነጋዴዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድር እንደነበር ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.