Fana: At a Speed of Life!

በኮሮናቫይረስ ክፉኛ የተጎዳችው የጣሊያኗ ሎምባርዲ ግዛት ጥብቅ እርምጃ ወሰደች

አዲስ አበባ፣መጋቢት 13፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)በጣሊያን ኮሮናቫይረስ የተቀሰቀሰባትና በቫይረሱ ክፉኛ የተጎዳችው የሎምባርዲ ግዛት የወረርሽኙን ስርጭትን ለመግታት ያስችላል ያለችውን ጥብቅ እርምጃዎች ወስዳለች፡፡

ሎምባርዴ ነዋሪዎቿ ለሳምንታዊ ግብይቶችና የግል ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ለማከናወንም ጭምር  በምንም ምክንያት ከቤታቸው መውጣት እንደማይችሉ አስታውቃለች።

የጣሊያኗ ግዛት ይህንን ጥብቅ መመሪያ ያስተላለፈችው በትናንትናው ዕለት ብቻ ጣልያን ስምንት መቶ  የሚሆኑ ሰዎችን በኮሮናቫይረስ ማጣትዋን ተከትሎ ነው ተብሏል።

በጣሊያን ከተመዘገበው  4 ሺህ 825 ሰዎች ሞት ውስጥ 3 ሺህ ዘጠና አምስት የሚሆነውበሎምባርዲ ግዛት  የተመዘገበ   ነው ተብሏል፡፡

የክልሉ ፕሬዝዳንት አቲሊዮ ፎንታና  ÷በሎምባርዴ ግዛት ሁሉም የንግዶች  እንቅስቃሴዎች ከአስፈላጊ የአቅርቦት በስተቀር  እንዲዘጉ መወሰኑን በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

ከዚያም ባለፈ በሆስፒታሎች ፣ በመንገዶች እና በባቡር ሐዲዶች ላይ ከሚሰሩት በስተቀር በግንባታ ቦታዎች ላይም ጭምር ሥራ ስራ እንዲቆም መታዘዙ ነው የተሰማው፡

ከሆስፒታል፣ ከመንገድና ባቡር ትራንስፖርት ባሻገር በክልሉ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንደማይኖር በመግለጫቸው ገልፀዋል።

በሌለም በኩል በትናንትናው እለት  የኢጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ÷ በሀገሪቱ ውስጥ  በጣም አስፈላጊ ያልሆኑ የንግድ ሥራዎችን  እንደሚቋረጡ ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን ሱፐርማርኬቶች፣ ፋርማሲዎች፣ ፖስታ ቤት ፣ ባንኮች እና የሕዝብ ትራንስፖርቶች ክፍት ሆነው እንደሚቀጥሉም ነው አስታውቀዋል።

በጣሊያን የወረርሽኙን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎች ቢወሰዱም በቫይረሱ የሚያዙ እና በወረርሽኙ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በእያደገ መምጣቱም ነው የሚነገረው፡፡

በአሁኑ ወቅት በመላው ጣሊያን በአጠቃላይ 53 ሺህ 578  ሰዎች  በቫይረሱ  የተያዙ ሲሆን ÷6 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ከበሽታው አገግመው መውጣታቸው ተነግሯል፡፡

እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን   ከ13ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.