Fana: At a Speed of Life!

በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሦስት ተጨማሪ ሰዎች ተገኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 89 ሰዎች ውስጥ ሦስት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።

ከዚህ ቀደም በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው የ85 ዓመት ኢትዮጵያዊ አዛውንት አገግመዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተገኙትን ሶስት ሰዎች ጨምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 38 እንዳደረሰው የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለጹት፤ ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሦስቱም ግለሰቦች የውጭ አገሮች ጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን፥ ሁሉም በአዲስ አበባ ይገኛሉ።

”የመጀመሪያው ግለሰብ የ29 ዓመት ወንድ ሲሆን መጋቢት 10 ቀን ከዱባይ የመጣና በበሽታ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበረው ነው” ብለዋል።

ሁለተኛው የ34 ዓመት ወንድ መጋቢት 23 ከዱባይ የመጣና በማቆያ የነበረና ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበረው መሆኑ ታውቋል።

ሶስተኛዋ የ35 ዓመት ሴት በመጋቢት 25 ከስውዲን የመጣችና በማቆያ የነበረች መሆኗን ገልጸዋል።

ዛሬ ከቫይረሱ ያገገሙትን የ85 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ በድምሩ አራት ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ከአዲስ አበበና ከአዳማ 641 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የተደረገላቸው መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህም 510 ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው እና የቀሪዎቹ ውጤት በቀጣይ እንደሚታወቅ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

 

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.