Fana: At a Speed of Life!

በኮሮና ቫይረስ የሚከሰተው በሽታ ስያሜ ተሰጠው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለሚከሰተው በሽታ “ኮቪድ -19” የሚል መጠሪያ መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ በኮሮና ቫይረስ የሚከሰተው በሽታ “ኮቪድ -19” የሚል መጠሪያ እንደተሰጠው ተናግረዋል።

ስያሜው ከየትኛውም መልክዓ ምድር፣ እንስሳ፣ ግለሰብም ሆነ ቡድን ጋር ግንኙነት እንደሌለውም አስረድተተዋል።

በቫይረሱ ሳቢያ የሚከሰተው በሽታ መጠሪያ “ኮሮና”፣ “ቫይረስ” እና “በሽታ” ከሚሉት ቃላት እና ቫይረሱ ከተከሰተበት የፈረንጆቹ “2019” የተወሰደ መሆኑም ተመላክቷል።

ኮሮና ቫይረስ የሚለው ስያሜ በሽታው የሚገኝበት የቫይረስ ቡድን መጠሪያ እንጂ የበሽታው የተለየ መጠሪያ አለመሆኑም ተገልጿል።

በቅርቡ በቻና ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ በተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ በላይ መድረሱ ተሰምቷል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.