Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ሶዶ አንዲት እናት አራት ልጆችን በሰላም ተገላገለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ኦቶና ማስተማሪያና ሪፌራል ሆስፒታል አንዲት እናት አራት ልጆችን በሠላም ተገላግላለች።

በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ዎሺዎቻ ዳቃያ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወይዘሮ ወርቅነሽ ብርሃኑ ካገባች ዓመት ያለፋት ሲሆን የመጀመሪያዋ እርግዝናዋ መሆኑን ገልጻለች።

በሆዷ የተሸከመችው ከሁለት በላይ መሆኑን የተረዳችው ወዲያው እንደነበር ትናገራለች።

በጊዜው አስፈላጊውን የቅድመ ወሊድ ጥንቃቄ አድርጋ እንደተዘጋጀች የምትናገረው ወይዘሮ ወርቅነሽ፤ አራት ልጆችና መገላገሏ እንዳስደሰታት ነው የምትገልፀው።

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሰቲ ኦቶና ማስተማሪያና ሪፌራል ሆስፒታል የእናቶች ክትትልና ወሊድ ክፍል ባለሙያዎች ጉዳዩን አስቀድመው በማወቃቸው በጥብቅ ጥንቃቄ ሲከታተሏት ነበር።

የቅድመ ወሊድ ክትትል ሲያደርጉላት የቆዩ ባለሙያዎች በእለተ ሰኞ ጥር 17 ከምሽቱ አራት ሰዓት ይህች እናት ወደ ተቋማቸው መምጣቷን ይገልፃሉ።

በሆስፒታሉ ይህ ክስተት የመጀመሪያ ነው ያሉት ዶክተር በላቸው ሾቴ በማህፀንና ፅንስ ክፍል እስፔሻሊስት ናቸው።

ከአራቱ ህፃናት ሶስቱ ወንዶች ሲሆኑ አራተኛዋ ሴት ናት መሆኗ ተገልጿል።

አዲስ ከተወለዱ ህፃናት የመጀመሪያው ከተወለደ ከ16 ሰዓት በኋላ ሕይወቱ ቢያልፍም የቀሩት ሶስቱና ወላድ እናት ባለሙያዎች እንክብካቤ በማድረጋቸው አሁን ላይ በሙሉ ጤንነት ይገኛሉ።

በመለሰ ታደለ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.