Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ሶዶ ከተማ በተከሰተው የእሳት አደጋ ዙሪያ ለተጎጂዎች ዘላቂ ድጋፍ ለመስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የደቡብ ክልል የተለያዩ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የወላይታ ዞንና የሶዶ ከተማ አመራር አካላት ትናንትና በወላይታ ሶዶ ከተማ የተከሰተው የእሳት አደጋ ያደረሰውን ጉዳት በመመልከት ቀጣይ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

አደጋው ያደረሰውን ጉዳት በመለየት ቀጣይ ዘላቂ ድጋፍ ለመሠጠት የሚያስችል ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር እንድሪያስ  በገበያው በተከሰተው አደጋ ሰለባ የሆኑ ነጋዴዎች ለረዥም ጊዜ ደክመውና ለፍተው ያፈሩት ሀብት በእንዲህ አይነት ሁኔታ ሲወድምባቸው የሚሰማቸው ሀዘን ጥልቅ መሆኑን ገልፀው የዞኑ አስተዳደርና መላው የወላይታ ህዝብ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖችን ለመደገፍ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡

ከተማዋ ከዚህ በፊት አራት ጊዜ እንዲህ አይነት ተመሳሳይ የእሳት አደጋ ማስተናገዷንና ይህም አምስተኛ ጊዜ የተከሰተ አደጋ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር እንድሪያስ ቀጣይ በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋምና ዘላቂ መፍትሔ ለመፍጠር አንድ አቢይና የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎችን በማቋቋም ከነገ ጀምሮ ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ከደቡብ ክልል የተለያዩ ቢሮዎች የመጡ ኃላፊዎችም የእሳት አደጋው ያደረሰውን ጉዳት ተዘዋውረው ከተመለከቱ በኋላ በከተማዋ በደረሰው አደጋ ማዘናቸውን ገልጸው የወላይታ ዞን አስተዳደርና እና የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር በአደጋው ምክንያት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ ለሚያደርጉት ተግባር የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ነው የገለጹት፡፡

በጌትነት ጃርሳ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.