Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ሶዶ ከ300 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመናፈሻ ፓርክ ለመገንባት የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በወላይታ ሶዶ ከ300 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመናፈሻ ፓርክ ለመገንባት አቶ ተስፋዬ ይገዙ የመሠረተ ድንጋዩን አስቀምጠዋል፡፡

በደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ ለከተማው ልማትና እድገት ትልቁን ድርሻ በሚወስደው ግዙፉ መናፈሻ ፓርክ ውስጥ ነው የመሰረተ ድንጋዩን ያስቀመጡት፡፡

የወላይታን ባሕል የሚገልፁ ስራዎችን በሚያካትተው ይህ መናፈሻ ፓርክ በ8 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ላይ የሚሰራ ይሆናል፡፡

የመናፈሻ ፓርክ ግንባታ ተጀምሮ የሚቆም ሳይሆን በሦስት አመታት የሚጠናቀቅ መሆኑንና ለከተማው ውበትና እድገት ወሳኝ መሆኑንም ተገልጿል፡፡

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መርክነህ ማለዳ በበኩላቸው÷ ሶዶ መናፈሻ ፖርክ በከተማው በጀት ለመገንባት ታቅዶ የአጀማመር ስራዎች መኖራቸውንም አብራርተዋል፡፡

በስነስርዓቱም ላይ የክልልና የዞን አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በማህሌት ኡኩሞ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.