Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ዞን ምርጫ በተደረገባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት እየተገለፀ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ አካል የሆነው ቀሪ ምርጫ በትላንትናው ዕለት መካሄዱ ይታወቃል፡፡
የዚህ ምርጫ ውጤት የድምጽ ቆጠራ ተደርጎ ዛሬ ማለዳ ላይ ለህዝብ ይፋ ተደርጓል።
ውጤት ሲመለከቱ የነበሩ መራጮች ትላንት ይወክለናል ላሉት ፓርቲ የሰጡት ድምጽ ይፋ በመደረጉ መደሰታቸውንና ምርጫው ሰለማዊ እንደነበረም ተናግረዋል።
እኛ መራጮች የሰጠነው ድምጽ በሁሉም የምርጫው ተዋንያን ሊከበርልን ይገባል ብለዋል።
የወላይታ ዞን ምርጫ ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ስምዖን በበኩላቸው÷ የድምጽ አሰጣጡ በተሳካ ሁኔታ ተደርጎ ቆጠራውም ማታ አልቆ ዛሬ በሁሉም ጣቢያዎች ውጤቱ ለህዝቡ ይፋ ተደርጓል ብለዋል።
በማስተዋል አሰፋ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.