Fana: At a Speed of Life!

በወንጀለኛ መቅጫና ማስረጃ ረቂቅ ህጎች ላይ የሚመክር መድረክ እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በወንጀለኛ መቅጫና ማስረጃ ረቂቅ ህጎች ላይ የሚመክር መድረክ እያካሔደ ነው።

የወንጀለኛ መቅጫና ማስረጃ ረቂቅ ሕጎች ከሰብዓዊ መብት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ተከታትሎ ለማስፈጸም የሚያስችል መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ የኢፌዴሪ ረቂቅ የወንጀለኛ ሕግ ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ መዘጋጀቱ ትልቅ እርምጃና ለዓመታት የታዩ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል ነውም ብለዋል።

ረቂቅ ሕጉ ከክስ ምስረታ እስከ ምርመራ፣ ከምርመራ እስከ ፍርድ አሰጣጥ ያሉ ሒደቶችንና የዳኝነት ሕጎችን የሚፈትሽ መሆኑንም ገልጸዋል።

ለሚቀጥሉት ረጅም ዓመታት ገዢ ሆኖ የሚቀጥል ረቂቅ ሕግ ስለሆነ በጥልቀት መወያየትና መስራት ያስፈልጋል ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ሕጉ ከሌሎች ሕጎች ጋር ተናባቢና ተጣጥሞ የሚሄድ መሆኑ መፈተሽ እንዳለበት ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ ረቂቅ ሕጎቹ የያዟቸው ዝርዝር ጉዳዮች በመድረኩ እየተዳሰሱ እንደሚገኙም ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Front page – Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C
fanabc.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.