Fana: At a Speed of Life!

በወጪ ንግድ ባለፉት ስድስት ወራት 21 በመቶ እድገት ተመዝግቧል – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወጪ ንግድ ባለፉት ስድስት ወራት 21 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ምላሽ የኤክስፖርት ዕድገቱ ባለፉት 20 ዓመታት ከተመዘገበው እንደሚልቅ ነው የተናገሩት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍኖተ ብልፅግና ሀገር በቀል ማሻሻያ የባለፉት ሶስት ዓመታት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ መሰረት ላይ ያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የብድር ጫና መቀነስ፣ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ማጠናቀቅ፣ ኤክስፖርት ማበረታት፣ ገቢን ማሳደግ፣ ገበያን ማረጋጋት እና የዕድገት ቀጣይኔን ማረጋገጥ የሚሉ ዋነኞች መሰረታዊ ሐሳቦችን የያዘ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ብድር ተበድራ ተጨማሪ ብድር መበደር የማትችልበት ደረጃ ላይ ደርሳ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡

ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት አለማጠናቀቅ የሀገር ኢኮኖሚ እንዳይንቀሳቀስ እግሩ እንዲታሰር አድርጎ ነበር

ይህ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሲዘጋጅ ኮቪድ አልነበረም ፣ይህም ኮቪድ ያስከተለው ጫና እንዳይካተት ማድረጉንም አንስተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ አንበጣ፣ ጎርፍ እና የፀጥታ ችግሮች ሀብትና ጊዜ እንዲባክን ማድረጋቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህም ለልማት መዋል የነበረበት በቢሊየን የሚቆጠር ብር ለእነዚህ ጉዳዮች እንዲውል ተደርገዋል ነው ያሉት፡፡

ሆኖም ይህንን ተቋቁሞ ባለፈው ዓመት 6 ነጥብ 1 በመቶ እድገት መመዝገቡን ነው የጠቀሱት፡፡

ለዕድገቱ ዋነኛ ምክንያቶች ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ በርካታ ሀገራት የተከተሉትን መንገድ አለመከተላችን ጫናው ከሌሎች አንፃር የከፋ እንዳይሆን አድርጎታል ነው ያሉት፡፡

ጥቅል እድገት ብቻ ሳይሆን በነፍስ ወከፍ ከ1 ሺህ ዶላር በላይ ጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት 100 ቢሊየን ብር መድረሱን አስረድተዋል፡፡

የነፍስ ወከፍ እና ጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት ወደየግለሰቡ ወርዶ በአጭር ጊዜ የሚታይ ነገር ላይ መጣ ይችላል ብለዋል፡፡

ጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት መጨመር ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢንቨስተር ለመሳብ እና ለሌሎች ጉዳዮች ላይም ጥቅም እንዳለው አንስተዋል፡፡

የንግድ ሚዛን በተመለከተ ከጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት አንጻር ሲታይ በ2010 ከዜሮ በታች ኔጋቲቭ 14 ነጥብ 7 እንደነበረ አንስተው በ2012 ኔጋቲቭ 12 ነጥብ 1 በመቶ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በ2012፤ 228 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን አንስተው ይህ መም ከባለፈው ዓመት አንጻር ሲታይ ከ30 ቢሊየን ብር በላይ ማስመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት ስምንት ወራት ውስጥ ደግሞ መንግስት 191 ቢሊየን በር መሰብሰቡን ጠቀሰዋል፡፡

ዓመታዊ በጀትን በተመለከተ 160 ቢሊየን መሆኑን ያስታወሱት ጠቅለይ ሚኒስትሩ ከባለፈው ዓመት አንጻር ሲታይ 36 ቢሊየን ብር መጨመሩን ነው ያስታወሱት፡፡
ግብርና፣ መንገድ ጤና ትምህርት ላይ ከ2010 አንጻር ሲታይ መሻሻሎች መኖራቸውንም አንስተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.