Fana: At a Speed of Life!

በወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባው የተመራ የሚኒስቴሩ የልዑካን ቡድን በድሬዳዋ ከተማ በመገኘት ከአመራሮች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የአካባቢው ሽማግሌዎች እና ከኢሳ ጎሳ መሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሰላም ሚኒስቴር የህግ ማስከበር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባው የተመራ የልዑካን ቡድን በድሬዳዋ ከተማ ተገኝቶ የዞንና ወረዳ አመራሮች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የአካባቢው ሽማግሌዎች፣ የኢሳ ጎሳ መሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

የልዑካን ቡኑ ከጥቂት ቀናት በፊት በአፋር ክልል በመገኘት በተመሳሳይ የማህበረሰብ እና አመራሮች ውይይት ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

በውይይቶቹ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎች እና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የሚበጁ ገንቢ አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡

ወ/ሮ ፍሬአለም የተነሱ ምክረ ሀሳቦችንና መጠይቆችን ተቀብለው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ሁላችንም መተባበር አለብን ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለሁላችንም የምትበቃ ትልቅና ውብ ሀገር ናትግጭት ሲፈጠር በተረጋጋና በሰለጠነ መንገድ መወያየት ይገባል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ኃይል መጠቀም በአስቸኳይ መቆም አለበት፤ አመራሩም በስርዓት ለህግ መከበር መቆም አለበት ነው ያሉት፡፡

አክለውም የወገኖቻችንን ጉዳት ልንቀብል አይገባም፤ ህጻናት የነገ የዚህች ሀገር ተስፋ ናቸውና ወደ ትምህርት ቤት መመለስ አለባቸው ብለዋል፡፡

እናቶች እንባቸው ሊታበስ ይገባል ያሉት ወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባው ለማህበረሰቡ የሚያስፈልጉ የንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ የመንገድ፣ የጤና አገልግሎት እንዲስፋፋ በአፋጣኝ በጋራ መስራ አለብን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመወያየትና በመደማማጥ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር ህዝብን ባማከለ መልኩ ችግሮች እንዲፈቱ ማድረግ ያስፈልገናል ብለዋል፡፡

መንግስት በቀጣይነት የቀጠናው ሰላም ዘላቂ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

በመጨረሻም የማህበረሰብ ተወካዮችን፥ የጎሳና የሃይማኖት መሪዎችን፥ አመራሩን እና በአጠቃላይ የውይቱን ተሳታፊዎችን ማመስገናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጀ ያሳያል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.