Fana: At a Speed of Life!

በዋግ ኽምራ ዞን ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የአተት ክትባት እንደሚሰጥ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዋግ ኽምራ ዞን ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የአጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት (አተት) ወረሽኝን አስቀድሞ ለመከላከል “ኢቪኮሆል” የተባለ ክትባት እንደሚሰጥ የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
በብሄረሰብ ዞኑ ከ88 ሺህ በላይ ተፈናቃይ ወገኖች የሚገኙ ሲሆን÷ በውሃ አቅርቦትና በንፅና ጉድለት ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን አተት ለመከላከል ክትባቱ እንደሚሰጥ ነው የተገለጸው፡፡
የአተት ክትባት ዘመቻ ከመጀመሩ አስቀድሞ በተካሄደው የንቅናቄ መድረክ ላይ የብሄረሰብ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ ስቡህ ገበያው÷ እንደ አካባቢያችን ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታ በርካታ ተፈናቃይ የህብረተሰብ ክፍል የሚገኝበት በመሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠንን ዕድል በመጠቀም ሊፈጠር የሚችለውን ወረሽኝ አስቀድመን ልንከላከል ይገባል ብለዋል፡፡
ሊከሰት የሚችልን ወረርሽኝ ለመከላከል ሁሉም በያለበት ተቀናጅቶ ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅበትም ነው ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪው ያሳሰቡት።
ክትባቱ 295 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ በሁለት ዙር የሚሰጥ ይሆናል መባሉን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.