Fana: At a Speed of Life!

በውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ ገብነትንና አላስፈላጊ ጫናን በምርጫ ካርድ የመቅጣት ዘመቻ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ በመግባትና አላስፈላጊ ጫና በመፍጠር ላይ የሚገኘውን የባይደን አስተዳደርና የዴሞክራት ፓርቲን በሜሪላንድ በምርጫ ካርድ ለመቅጣት ያለመ ዘመቻ በይፋ ተጀመረ።
የአሜሪካ ኢትዮጵያ ፐብሊክ ጉዳዮች ኮሚቴ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን በሜሪላንድ ምርጫ የባይደን አስተዳደርን ለመቅጣት እንቅስቃሴው መጀመሩን ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
በፈረንጆቹ አዲስ አመት በሚካሄደው የሜሪላንድ የመካከለኛ የምርጫ ጊዜ በሚካሄደው ምርጫ ከኮሚቴው ጋር በመሆን ሃያ የኢትዮ-አሜሪካ ማህበረሰብ ጥምረቶችና የቢዝነስ ተቋማት ዘመቻውን እንደሚመሩት በመግለጫው ተመልክቷል።
በዚህም ኮሚቴው፣ የኢትዮ-አሜሪካ ማህበረሰብ ጥምረትና አጋር አካላት ቤት ለቤት በመሄድ እንዲሁም ስልጠናዎችን በመስጠት በምርጫው ላይ የማንቃት እንቅስቃሴ እንደሚሰሩ ተገልጿል።
የአሜሪካ ኢትዮጵያ ፐብሊክ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀ መንበር መስፍን ተገኑ እንዳሉት፥ ዘመቻው ከሲቪክ ማህበራት ጋር በመተባበር እንዲሁም በጎ ፍቃደኞችን በመቅጠርና ተመሳሳይ አጀንዳ ካለቸው አካላት ጋር ጥምረት በመፍጠር ይመራል።
የኢትዮ-አሜሪካ የረጅም ጊዜ ወዳጅነትና የሁለትዮሽ ግንኙነትን አስታውሰው፤ ከአጋር አካላት ጋር በመሆንም ድምጻችንን የሚሰማ አካልን ወደ ስልጣን በማምጣት የጋራ ተጠቃሚነት እንዲሰፍን እንሰራለን ብለዋል።
ከዚህ ቀደም በቨርጂኒያ የመካከለኛ ጊዜ ምርጫ በግዛቷ የሚገኙ ኢትዮ-አሜሪካውያን የዴሞክራት ፓርቲንና የባይደን አስተዳደርን በምርጫ ካርዳቸው ለመቅጣት ተግባራዊ እንቅስቀሴ ማድረጋቸው ይታወሳል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.