Fana: At a Speed of Life!

በውጭ አገር የስራ ዕድል ፈጠራ እና በቱሪዝም ብራንድ “ምድረ ቀደምት” ዙሪያ  የበይነ መረብ ስልጠና ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በውጭ አገር የስራ ዕድል ፈጠራ እና በቱሪዝም ብራንድ “ምድረ ቀደምት” ዙሪያ  ለአምባሳደሮችና ዲፕሎማቶችየበይነ መረብ ሥልጠና ተሰጠ።

የቱሪዝም ምርቶችን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ኢትዮጵያ  በዘርፉ የተሻለ የውጭ ምንዛሪ እንድታገኝና በሴክተሩ የሚፈጠረውን የስራ ዕድል ለማሳደግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የቱሪዝም ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ስራ በተናበበ መልኩ ለመስራት የሚያስችል ስልጠና ተሰጥቷል።

በዚህም የኢትዮጵያ  የቱሪዝም ብራንድ  “ምድረ ቀደምት”ን  በሚመለከት የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ  አቶ ስለሺ ግርማ  እንዲሁም በውጭ አገራት የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ በሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር  አቶ ንጉሱ ጥላሁን   ለኢትዮጵያ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በበይነ መረብ  ስልጠና ሰጥተዋል።

አቶ ንጉሱ በስልጠናው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ ያላትን ዕምቅ የቱሪዝም ሀብት ለተቀረው አለም በማስተዋወቅ የቱሪዝም ኢንዱስትሪው ለአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ መንግስት ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል።

አያይዘውም  በአገር በቀል ኢኮኖሚ ፍሮተ ካርታ  ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል አንዱ የቱሪዝም ዘርፍ እንደሆነ ጠቅሰው÷የቱሪዝም ዘርፉ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል እየፈጠረ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

በተጨማሪም የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን የተቋቋመባትን  ፣ የኮሚሽኑ የ10 ዓመት ፍኖተ ካርታ እና የአምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ እና በውጭ አገር  የሥራ ስምሪት  በተመለከተ ኢትዮጵያውያን  ተጠቃሚ መሆን በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ከአምባሳደሮችናዲፕሎማቶቹ የሚጠበቁ ዋና ዋና ጉዳዮች አስመልክተው አቶ ንጉሱ ገለፃ አድርገዋል።

የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ  አቶ ስለሺ ግርማ  በበኩላቸው÷የቱሪዝም ዘርፉ ለአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ  እያደረገ እንደሚገኝ አንስተዋል።

ከዘርፉ ሊገኝ የሚችለውን ጥቅም ይበልጥ ለማሳደግ በባለድርሻ አካላት መካከል የተናበበና ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር ስለሚያስፈልግ ሚሲዮኖቻችንም እያደረጉ ያለውን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ  ጠይቀዋል፡፡

በተጨማሪም የአገራችን የቱሪዝም ብራንድ “ምድረ ቀደምት”/Ethiopia “Land of Origins” ዙሪያ በፓወር ፖይንት የተደገፈ ዝርዝር ገለፃ በቱሪዝም ኢትዮጵያ ተደርጓል።

የስልጠና ተሳታፊዎችም በኢትዮጵያ  የቱሪዝም ብራንድ ላይ ተመሳሳይ ግንዛቤ በመያዝ፣ ወቅታዊና በተናበበ መልኩ ለተቀረው አለም ለማስተዋወቅ እንደሚያግዛቸው መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.