Fana: At a Speed of Life!

በዓለምአቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው ኢትዮጵያዊው ታዳጊ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ናትናኤል ሙሉጌታ የተባለ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ በካምብሪጅ ዓለምአቀፍ ፈተና ከፍተኛውን ውጤት አስመዘገበ።

ነዋሪነቱ በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን የሆነው የ16 አመቱ ታዳጊ ናትናኤል የ2021 የካምብሪጅ አለማቀፍ ፈተናን በመውሰድ ነው እጅግ ከፍተኛ የተባለውን ነጥብ ያስመዘገበው።

ናትናኤል በተፈተነባቸው የትምህርት አይነቶች በሁሉም ኤ (ከፍተኛ ውጤት) ያስመዘገበ ሲሆን÷ ከነዚህ ውስጥም በሰባት የትምህርት አይነቶች ኮከብ(*/እጅግ ከፍተኛ ውጤት) ማስመዝገብ ችሏል።

በአለም አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ማምጣቱ ለቀጣይም የሚያነቃቃው እንደሆነ እና ወደፊት የሚወዳትን ሃገሩ ኢትዮጵያን ማገልገል እንደሚፈልግ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።

የናትናኤል ወላጅ አባት ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ፊታሞ÷ ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን እንዲወዱ አድርገው ማሳደግ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

የካምብሪጅ አለማቀፍ ፈተና በእንግሊዝ ፣ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ኒውዝላንድ እና ደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው የተማሪዎች ብቃት መመዘኛ ፈተና ነው።

በሞሊቶ ኤልያስ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.