Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ላይ የትምህርት፣ ባህልና ቱሪዝም ዘርፎችን ታሳቢ ያደረገ የኮቪድ19 ክትባት አቅርቦት ሊኖር ይገባል-የትምህርት ሚኒስትሩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) 211ኛ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ ስብሰባ በበይነ መረብ እየተካሄደ ነው።

በዩኔስኮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት እና የዩኔስኮ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል እንዲሁም የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ በስብሰባው ላይ በመካፈል ላይ ይገኛሉ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ባደጉት ንግግር ኢትዮጵያ በትምህርት፣ በሳይንስ፣ በባህልና ቱሪዝም ዘርፎች በማከናወን ላይ ያለችውን ዓበይት ተግባራት ጠቅሰዋል።

ከኮቪድ19 በኋላ የትምህርት ዘርፉን ዳግም ለመክፈትና ለማስቀጠል በመንግስት የተወሰዱ እርምጃዎችን፣ በቱሪዝም ዘርፍ ያለውን የጎብኚዎች ፍሰት እንዲሁም በትግራይ ክልል ህግን ለማስከበር ከተደረገው ዘመቻ ጋር ተያይዞ በዩኔስኮ በተመዘገቡ ቅርሶች  ደህንነት ዙሪያም ገለፃ አድርገዋል።

በጫና ውስጥ ያለውን  የቱሪዝም ዘርፉ ለማነቃቃት መንግስት አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን  በመገንባት እና ክፍት በማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየሰራ መሆኑን እና አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችም በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በሁሉም የዓለም ሀገራት የትምህርት ፣ የባህልና የቱሪዝም ዘርፍን ከጤና ባለሙያዎች ቀጥሎ ታሳቢ ያደረገ የክትባት አቅርቦት ሊኖር ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ኮቪድ19 በጤናው ዘርፍ ላይ ያስከተለውን ጫና በንግግራቸው የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ በተለይም በኮቫክስ የኮቪድ ክትባት አቅርቦት የዓለም አቀፍ የተራድዖ ግብረ-ሀይል በተሰጠ ድጋፍ በኢትዮጵያ ክትባት መሰጠት መጀመሩ መልካም ቢሆንም እስከ ታህሳስ 2014 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ 20 በመቶ የሀገሪቱን ዜጎች ብቻ ተደራሽ የሚያደርግ ሀብት ብቻ መገኘቱ አዝጋሚ መሆኑን አንስተዋል።

በተቃራኒው ያደጉት ሀገራት ከፍተኛ የክትባት ክምችት ላይ መሰማራታቸው ተገቢ አለመሆኑን የዩኔስኮ ቦርድ ድምፁን እንዲያሰማ ሚኒስትሩ መጠየቃቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

በ211ኛው የዩኔስኮ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ ስበሰባ ላይ ከሚኒስትሩ በተጨማሪ በፈረንሳይና በዩኔስኮ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ የአፍሪካ ሀገራትን በመወከል እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ ከሰሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራትን በመወከል የዩኔስኮ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆና በማገልገል ላይ ትገኛለች።ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.