Fana: At a Speed of Life!

በዓለም በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 22 ሺህ ደርሷል

አዲስ አበባ ፣መጋቢት 17፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 22 ሺህ 30 መድረሱ ተገልጿል።

በቅርቡ በቻይና ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አሁን ላይ 170 በሚሆኑ የዓለም ሀገራት ውስጥ መስፋፋቱ ተነግሯል።

በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥርም 22 ሺህ 30 መድረሱን ጆን ሆፕኪንሰ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

በዚህ መሰረትም የኮሮና ቫይረስ ክፉኛ እየጎዳት የምትገኘው ጣሊያን 7 ሺህ 503 የሚሆኑ ዜጎቿ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል።

ከዚህ ባለፈም በስፔን 3ሺህ 647፣በቻይና 3 ሺህ 119፣ በኢራን 2 ሺህ 77፣ እና በፈረንሳይ 1 ሺህ 331 ዜጎች በኮሮና ቫይረስ  ህይወታቸው ማለፉ ነው የተገለጸው።

በአሜሪካ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ወደ 1ሺህ 50 ከፍ ሲል፥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 70 ሺህ ደርሷል።

ቫይረሱ በዓለም አቀፍ ደረጃ  በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋቱን ተከትሎም ሀገራት የተለያዩ የመከላከያ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

በዚህ መሰረትም በርካታ ሀገራት ድንበራቸውን ከመዝጋት ባለፈ ወደ ተለያዩ ሀገራት ያደርጉት የነበረውን በረራ ላልተወሰነ ጊዜ አግደዋል።

ከዚህ ባለፈም ሀገራቱ  የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ዜጎች ቤታቸው እንዲቆዩ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ ከዓለም ህዝብ ሩብ የሚሆነው ቤት ውስጥ መቀመጡን መረጃዎች ያሳያሉ።

ምንጭ፥ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.