Fana: At a Speed of Life!

በዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ10 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ10 ሚሊየን አልፏል፡፡

በዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 10 ሚሊየን 87ሺህ 830 የደረሰ ሲሆን÷ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 501 ሺህ 466 መሆኑ ታውቋል፡፡

5 ሚሊየን 466 ሺህ 329 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገም ችለዋል ነው የተባለው፡፡

እንደ ጆን ሆፕኪንስ መረጃም በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር አሜሪካ ቀዳሚ ስትሆን 2 ሚሊየን 596 ሺህ 770 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

በመቀጠልም ብራዚል ከፍተኛ ቁጥር እያስመዘገበች ሲሆን 1ሚሊየን 315 ሺህ 941 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል፡፡

በተመሳሳይ ሩሲያ ቫይረሱ የበረታባት ሃገር ስትሆን በሃገሪቱ 1ሚሊየን 627 ሺህ 646 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

እንዲሁም በአሜሪካ 128 ሺህ 152፣በብራዚል 57 ሺህ 103፣በሩሲያ ደግሞ 8 ሺህ 969 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በተጨማሪም በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 359 ሺህ ያለፈ ሲሆን ÷172ሺህ 974 ሰዎች ደግሞ ማገገም ችለዋል ተብሏል፡፡

ከ9 ሺህ 283 የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.