Fana: At a Speed of Life!

በዓለም በኮቪድ19 ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ19 ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን አልፏል፡፡

እስካሁን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ168 ሚሊየን 535 ሺህ በላይ ሲሆን፥ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

አሜሪካ፣ ህንድ፣ ብራዚል፣ ፈረንሳይ እና ቱርክ ቫይረሱ ከጸናባቸው ሃገራት መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡

በአፍሪካ እስካሁን ከ4 ሚሊየን 771 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፥ ከ128 ሺህ 900 በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮ፣ ቱኒዝያ፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽ ከአህጉሪቱ ቫይረሱ የጸናባቸው ሃገራት በመሆን በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በአንጻሩ በዓለም ከ150 ሚሊየን በላይ ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ፥ በአፍሪካም ከ4 ሚሊየን 283 ሺህ በላይ ሰዎች አገግመዋል፡፡

ምንጭ፡- ዎርልድ ኦ ሜትር እና ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.