Fana: At a Speed of Life!

በዓለም የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 29 ሚሊየንን ተሻገረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለም ዙሪያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ29 ሚሊየን ማለፉን የወርልድ ኦ ሜትር መረጃ ያሳያል።

እንደ መረጃው በዓለም አቀፍ ደረጃ እስካሁን 29 ሚሊየን 185 ሺህ 779 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በአለም በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለአለም ስጋት መሆኑን ቀጥሏል።

እንደ ወርልድ ኦ ሜትር መረጃ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እስካሁን የ928 ሺህ 287 ሰዎች ህይዎት አልፏል።

ከ21 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸውን መረጃው ያመላክታል።

አሜሪካ፣ ህንድ፣ ብራዚል፣ ሩሲያ እና ፔሩ በአለም ከፍተኛ የቫይረሱ ተጠቂ ሰዎችን የያዙ አገራት በመሆን ከአንድ አስከ አምሰተኛ ደረጃን መያዛቸውን ቀጥለዋል፡፡

ለረዥም ጊዜ በአምስተኛ ደረጃ የነበረችው ደበብ አፍሪካ በአጠቃላይ 649 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘውባት ከኮሎምቢያ እና ሚክሲኮ በመቀጠል በስምንተኛ ደረጃ ተቀምጣለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.