Fana: At a Speed of Life!

በዓሉን ያከበርነው የክልሎችን የህዝብ ለህዝብ ትስስር ባጠናከረ መልኩ ነው – አፈ ጉባኤ አቶ ሰለሞን

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ሰለሞን ላሌ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን ስናከበር የክልሎችን የህዝብ ለህዝብ ትስስር ባጠናከረ መልኩ እንዲሆን ትኩረት ሰጥተናል ሲሉ ተናገሩ።

በሲዳማ ክልል ምክር ቤት አዘጋጅነት 15ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የማጠቃለያ መርሃ ግብር በሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል፡፡

ባለፉት ስምንት ቀናት በዓሉ በክልሉ ሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በፓናል ውይይት፣ ለመከላከያ ሠራዊት ደም በመለገስ፣ በፅዳት ዘመቻና በሌሎችም መርሃ ግብሮች ሲከበር ቆይቷል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጨፌ ኦሮሚያ ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ የህወሓት ጁንታ በሚከተለው ተንኮልና ሴራ የተሞላበት ሥርዓት ህዝቡ ብዙ መከራ ማስተናገዱን ነው የገለጹት።

ሆኖም እውነተኛ የዴሞክራሲ ስርዓት ተግባራዊ እንዲሆን የለውጡ አመራሮች ባሳዩት ቁርጠኝነትና ትጋት የሲዳማ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄው ምላሽ ማግኘቱን አስታውሰዋል።

በቀጣይ ሁሉም ዜጋ ጁንታው የዘራውን የብሄር ጥላቻንና ግጭትን በማስቀረት ለሀገሪቱ የብልፅግና ጉዞ መሳካት እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ከእነችግሮቹም ቢሆን በማንነታችን ሳንሸማቀቅ በአደባባይ እንድናከብር ያደረገን በዓል ስለሆነ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
377
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.