Fana: At a Speed of Life!

በዛሬው ዕለት በሁሉም ግንባሮች በህወሐት ውስጥ ያለውን ቡድን ፍላጎት ማክሸፍ ተችሏል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በህወሐት ውስጥ ባለ ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ በዛሬው ዕለት የተወሰደውን እርምጃ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስት በመግለጫቸው ተስፋ የቆረጠው እና ከሃዲው የህወሃት ቡድን ያልታሰበ ፤ የማይጠበቅ ጥቃት በመፈፀም ኪሰራ ሊያደርስ እንደነበረ ገልፀዋል።
 
ጦርነት በሀገሪቱ ላይ እንዳይከሰት መንግስት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም በህወሃት ውስጥ ያለው ቡድን ከንቱ አስቀርቶታል ብለዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ የትግራይ ክልል ልዩ ሀይል አባላት እና ሚሊሻዎች ፍትሃዊ ባልሆነው ጦርነት ላይ ላለመሳተፍ ጥረት ከማድረጋቸው ባሻገር ከሃዲውን ቡድን ክደው ወደ ሚቀርባቸው ክልል በሠላም ተቀላቅለዋል።
 
የአማራ ክልል ልዩ ሀይል እና ሚሊሻዎችም ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን የተሰነዘውን ጥቃት በብቃት መመከታቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
 
መከላከያ ሰራዊቱ በሁመራ ፣ ዳንሻ እና ቀራቅር በነበረው ውጊያ የጀግንነት ተግባራ መፈፀሙን ነው የገለፁት።
 
በዛሬው ዕለትም በሁሉም ግንባሮች በህወሐት ውስጥ ያለው ቡድን ያደረጋቸው ሙከራዎች መክሸፋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.