Fana: At a Speed of Life!

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን በዘላቂነት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን በዘላቂነት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የፌዴራል የከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ገለጸ።

ከስምንት ክልሎችና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ የአንድ ማዕከል እና ለዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ ባለሙያዎች በምክርና ድጋፍ ላይ ትኩረት ያደረገ የአሰልጣኞች ስልጠና በአዳማ ከተማ ተሰጥቷል፡፡

በፌዴራል ኤጀንሲዉ የዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቸሩ ኃ/ጊዮርጊስ÷ በከፋ ድህነት ውስጥ የነበሩ በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት እየተሳተፉ የሚገኙ ዜጎችን ኑሮ በዘላቂነት ለማሻሻል ስልጠናና የተለያዩ ድጋፎች እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም ለእነዚህ ዜጎች ከአካባቢ ልማት ስራ ጎን ለጎን በዘላቂነት ኑሯቸውን ማሻሻል የሚያስችሉ፤ ቁጠባ፣ ምክርና ድጋፍ፣ መሰረታዊ የቤተሰብ ትምህርት/ልምምድ፣ የባህሪ እና ክህሎት የመሳሰሉ ስልጠናዎች እንደየ ደረጃቸው እየተሰጠ ይገኛልም ነው ያሉት ፡፡

የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዙር የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች የቆይታ ጊዜያቸውን ስላጠናቀቁ ከፕሮጀክቱ የሚለቀቀውን የ500 ዶላር ድጋፍና በቆይታቸው በቁጠባ ያጠራቀሙት ገንዘብ እንደመነሻ ካፒታል እየተጠቀሙ በአካባቢያቸው ባገኙት የስራ አማራጭ እንዲሰማሩ የአንድ ማዕከል፣ የኑሮ ማሻሻያ እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ሊያደርጉላቸው እንደሚገባ መገለጹን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.