Fana: At a Speed of Life!

በየካ ክፍለ ከተማ መሬት ውስጥ ተቆፍሮ የተቀበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በየካ ክፍለ ከተማ መሬት ውስጥ ተቆፍሮ የተቀበረ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ እና ሽጉጥ በህዝብ ጥቆማ ተያዘ፡፡
የጦር መሳሪያዎቹ የተያዙት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ልዩ ቦታው ጨርቆስ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡
አጠራጣሪ ነገሮችን በትኩረት እየተመለከተና መረጃና ጥቆማዎችን ለፖሊስ እየሰጠ የሚገኘው የከተማ ነዋሪ ለእነዚህ የጦር መሳሪያዎች መገኘትም የጎላ አስተዋፅዖ ማበርከቱ ተመላክቷል፡፡
ፖሊስ በተጠቀሰው አካባቢ በሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ባደረገው ብርበራ አንድ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ ከ28 መሰል ጥይት ጋር እንዲሁም አንድ ሽጉጥ ከመሰል 28 ጥይት ጋር መሬት ውስጥ ተቆፍረው ከተደበቁበት ሊያገኛቸው ችሏል፡፡
የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ቲም ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ካሳሁን ተሾመ በህዝብ ጥቆማ የሚደረጉ ብርበራዎች ውጤት እየተገኘባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም ለከተማዋ ስጋት የሚሆኑ ጉዳዮችን ለማስወገድ እና የተላላኪ ባንዳዎችን እኩይ ሴራ ለማክሸፍ የህብረተሰቡ ጥቆማ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.