Fana: At a Speed of Life!

በየዘርፉ የተነሱ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት አመራሩ በቅንጅት መሥራት እንዳለበት ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በየዘርፉ የተነሱ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት አመራሩ በቅንጅት መሥራት አለበት ሲሉ የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ አሳሰቡ፡፡
የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሕዝብን አንገብጋቢ ጥያቄ ለመፍታት በየዘርፉ የተቋቋመውን ኮሚቴ የ90 ቀን ዕቅድ አፈፃፀም ገምግሟል፡፡
ከትራንስፖርት አገልግሎት ጋር በተያያዘ÷ የሐረሪ ክልል መንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አዲሱን ታሪፍ ስራ ላይ አንዲውል ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በተደረገው ውይይት መሰረት ወደ ስራ መገባቱ ተገልጿል፡፡
የነዳጅ አቅርቦት ችግር መፍትሔ እንዲያገኝና በዘርፉ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማስቀረት ከባለንብረቶች ጋር ውይይት መደረጉም ተመላክቷል፡፡
የሲሚንቶ አቅርቦትን በተመለከተም÷ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እንዲኖር ምክንያት የሆኑ ሁኔታዎችን ለማስቀረት እስከ ፋብሪካ በመሄድ ምክክር ተደርጎ ለህብረተሰቡ በቅናሽ ዋጋ ለማቅረብ እንዲቻል እየተሠራ ነው ተብሏል፡፡
ከኤረር አስፓልት ግንባታ ጋር በተያያዘም በሕጉ መሰረት ለህብረተሰቡ የካሳ ክፍያው ተፈጽሞ ወደ ሥራ እንዲገባ በልዩ ትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ÷ አመራሩ የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት በቁርጠኝነትና በቅንጅት እንዲሠራ አሳስበዋል፡፡
የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለማስቀጠል በሚፈለገው ጥራት እና ፍጥነት እንዲሠራ የባለድርሻ አካላት ክትትል እና ቁጥጥር እንዲጠናከር መጠየቃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.