Fana: At a Speed of Life!

በደሴ ከተማ ” ኑ አብረን በጋራ እናፍጥር” በሚል መሪ ቃል ታላቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ ፒያሳ ጎዳና ታላቅ የኢፍጣር መርሃ ግብር ተካሂዷል ።
በመርሃ ግብሩ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የእስልምና እምነት አባቶችና የእምነቱ ተከታዮች ተሳትፈዋል፡፡

 

የደሴ ከተማ ህዝባዊ መጅሊስ ሰብሳቢ ሼህ እንድሪስ በሽር ÷ ታላቁ የኢፍጣር መርሃ ግብር የተዘጋጀው በጦርነቱ ምክንያት ህዝባችን ላይ የደረሰውን የስነልቦና ስብራት በማከም ወደነበረበት ልዕልና ለመመለስና የከተማችን ህብረተሰብ የሚታወቅበትን አንድነትና አብሮነት ማጽናትን አላማ አድርጎ ነው ብለዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው÷መርሃ ግብሩ መልካም እሴቶችን የሚያጎለብት በመሆኑ ማህበራዊ ቅርርብ ለመፍጠር ሚናው የጎላ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ የክርስትና እምነት ተወካዮችም በመርሃ ገብሩ ተገኝተው “የኢፍጣር መርሃ ግብሩ አብሮነታችንን የሚያጎለብትና የወሎን ተምሳሌትነት በአደባባይ የምናሳይበትን እድል የፈጠረ ነው” ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተውናል።

በሌላ በኩል መንግስት የዘንድሮውን የረመዳን ወር በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች በኢትዮጵያ እንዲያከብሩ ባቀረበው ጥሪ መሠረት ‘ከዒድ እስከ ዒድ’ በሚል መሪ ሐሳብ ወደ ደሴ ከተማ የሚመጡ እንግዶችን ለማስተናገድ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

በዘሩ ከፈለኝ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.