Fana: At a Speed of Life!

በደሴ ከተማ  የተገነባው ጢጣ ፒፒ  ከረጢት ፋብሪካ ተመርቆ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ  80 ሚሊዮን ብር ወጭ  የተገነባው ጢጣ ፒፒ ከረጢት ፋብሪካ ተመርቆ ዛሬ ስራ ጀምሯል፡፡

ፋብሪካው አሁን ላይ በቀን 17 ሺ ከረጢት የሚያመርት  ሲሆን  በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ በቀን 74 ሺ ከረጢት ያመርታል።

በምርት ሂደት የሚፈጠረውን ተረፈ ምርት እንደገና ለመጠቀም የሚያስችል ቴክኖሎጂም ተገጥሞለታል።

ከአንድ ወር በፊት የሙከራ ምርት የጀመረው ፋብሪካው ለ200 ሰራተኞች የስራ እድል ተፈጥሯል፡፡

ጢጣ አካባቢ ሀጂ ሙክታር ይመር በተባሉ ባለሀብት የተገነባው የፕላስቲክና  ከረጢት  ፋብሪካው በ2006 ዓ.ም  ነበር ግንባታው የተጀመረው፡፡

በሙሉቀን  አበበ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.